ከቱሪዝም ዘርፍ ሊገኝ ከታሰበው የውጭ ምንዛሪ የ7.4 ሚሊዮን ዶላር ጉድለት መመዝገቡ ተገለጸ

ኢሳት (ህዳር 1 ፥ 2009)

ባለፉት ሶስት ወራቶች ብቻ ከቱሪዝም ዘርፍ ሊገኝ ከታሰበው የውጭ ምንዛሪ የ7.4 ሚሊዮን ዶላር (150 ሚሊዮን ብር አካባቢ) ጉድለት መመዝገቡን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሃሙስ ይፋ አደረገ።

ባለፈው አመት በኦሮሚያ ክልል ሲካሄድ የቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ ለገቢው መቀነስ ምክንያት መሆኑን የገለጸውን ሚኒስቴር በአመት ሊገኝ ይችላል ተብሎ ከሚጠበቀው ገንዘብ ከ400 ሚሊዮን ዶላር በላይ ጉድለት ሊያጋጥም እንደሚችል አመልክቷል።

በተያዘው በጀት አመት ከቱሪዝም ዘፍ ሶስት ቢሊዮን ዶላር ይገኛል ተብሎ ቢጠበቅም፣ በሃገሪቱ ባለው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ምክንያት ገቢው ያሽቆለቁላል ተብሎ ይጠበቃል።

ባለፈው ሶስት ወራቶች ተገኝቷል ከተባለው ገንዝብ የ 7.4 ሚሊዮን ዶላር ጉድለት እንደተመዘገበበት የባልህና ቱሪዝም ሚኒስተሪ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን ገልጿል።