የአልሸባቡ መሪ ኢትዮጵያ ጦሩዋን ከሶማሊያ ያስወጣችው በውስጥ ችግሯ ምክንያት ነው አሉ

ጥቅምት ፳፫ (ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- ሃሰን ያቆኡብ የተባሉት የአልሸባብ መሪ እንደገለጹት ኢትዮጵያ ሶማሊያ ውስጥ ይዛው የቆየችውን 8 ቦታዎች ለመልቀቅ የተገደደችው በውስጥ በተፈጠረባት የውስጥ ችግር አማካኝነት ነው ።

የታጣቂው ቡድን መሪ ኢትዮጵያ አገሪቱን ጥላ በመውጣቷ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል። የኢህአዴግ መንግስት በበኩሉ በአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ስም ያልሆነውን ጦር ለማውጣት የተገደደው በገንዘብ እጥረት ምክንያት መሆኑን ገልጿል።

ኢትዮጵያ ሩድ ዱሃሪ፣ ቡር ዱክሲሊ፣ ጋራስ ወይኒና ታይግሊው፣ ቡዱቡድ ጋላሳድ፣ ሞኮሪ፣ ሲል ካሊ እና ሃላጋን የተባለሉት ቦታዎች ለአልሸባብ በማስረከብ ጦሩዋን ከአገሪቱ አስወጥታለች።

ኢሳት በሶማሊያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች ትእዛዝ አንቀበልም መላታቸውንና በመቶዎች የሚቆጠሩም አመጽው ወደ አገራቸው አለመመለሳቸውን መዘገቡ ይታወቃል።