በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ችግር እየደረሰባቸው መሆኑን ተናገሩ

ጥቅምት ፲፭ (አሥራ አምስት ) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያኑ ለኢሳት እንደገለጹት፣ የሱዳን መንግስት ኢትዮጵያውያንን በዘፈቀደ እያሰረ ከፍተኛ ገንዘብ ይቀበላል። ከኢህአዴግ የደህንነት አባላት ጋር በመነጋገርም፣ ገዢውን ፓርቲ ይቃወማሉ የተባሉትን እያፈነ ወደ ኢትዮጵያ ይልካል።

ፍትህ አጥተን እየተሰቃየን ነው የሚሉት ኢትዮጵያውያን ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በእስር ቤት ውስጥ እየተሰቃዩ ቢሆንም፣ ድምጻቸውን የሚያሰማላቸው አካል ማጣታቸውን ገልጸዋል።