ጥቅምት ፲፭ (አሥራ አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የአፍሪካ ዳሬክተር ሃላፊ የሆኑት አቶ አበበ አዕምሮ ሥላሴ የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ እድገት ሕዝባዊ አመፁን ተከትሎ መዳከሙን ገልጸዋል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተግባር በግልባለሃብቶች ኢንቨስትመንት ፣ በውጪ ላኪዎች እና በውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፍሰት ላይ አሉታዊ ጫና ማሳደሩን የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ ገዢው ፓርቲ አስቸኳይ ሰላማዊ መፍትሄ ካልፈለገ የአገሪቱ ኢኮኖሚ አደጋ ውስጥ እንደገባ ይቀጥላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።