የሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ትምህርት ለመጀመር ፈቃደኛ አልሆኑም

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- የዩኒቨርስቲው ሴነት ተማሪዎች ጥቅምት 7 ትምህርት እንደሚጀምሩ አስታውቆ የነበረ ቢሆንም፣ ተማሪዎቹ ግን አንማርም በማለት ውጭ እንደሚውሉ የገለጸው  ወኪላችን፣ የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ፕ/ር ጨመዳ እና ምክትላቸው ዶ/ር በላይ ተማሪዎችን ሲለምኑ ታይተዋል።

በርካታ የታጠቁ ወታደሮች በግቢው ዙሪያ በተጠንቀቅ እርምጃ ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውንም ወኪላችን ገልጿል። በሃረር ከተማም ደግሞ ካድሬዎች ቤት ለቤት እየዞሩ ዲሽ ሲያስነቅሉ መዋላቸው ታውቋል። ለምን ብለው የሚጠይቁ ዜጎች ፣ አዋጁ ዲሽ እንዲነቀል ያዛል የሚል መልስ የሚሰጣቸው ሲሆን፣ ዲሾቻቸውን ለማውረድ ያንገራገሩ በሽብርተኝነት ተፈርጀው እርምጃ ይወሰድባቸዋል።