በምዕራብ አርሲ በርካታ ነጋዴዎችና ወጣቶች ታሰሩ

ጥቅምት ፬ (አራት) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :-በቢሾፍቱ ከደረሰው እልቂት በሁዋላ ከፍተኛ ህዝባዊ አመጽን ባስተናገዱት አጄና አጎራባች ከተሞች የሚገኙ የአገር ሽምጋሌዎች፣ ነጋዴዎች፣ ምሁራን፣ ባለሀብቶችና ወጣቶች ተይዘው መታሰራቸው ታውቋል።

ኢሳት እና ኦኤም ኤንን የሚመለከቱ ሰዎች እየተደበደቡ ወደ እስር ቤት የሚወሰዱ ሲሆን፣ ዲሾቻቻውም እንዲነቀል ተደርጓል።

ከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት አሁንም በአካባቢው ሰፍሯል። ባለፈው ሳምንት በዚህ ዞን በተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ሳይገደሉ እንዳልቀሩ የአካባቢው ነዋሪዎች መግለጻቸው ይተወሳል።