ፖሊሶች ዲሽ ሲያስወርዱ መዋላቸውን ከተለያ  አካባቢዎች የሚደርሱን መረጃዎች አመለከቱ

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :-የአሽኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀ ማግስት ፖሊሶች በተለይ በኦሮምያና በአማራ አንዳንድ ከተሞች ጣራ ላይ እየወጡ ዲሽ ሲያወርዱ ታይቷል። ኢሳትንና ሌሎችን የውጭ ሚዲያ ይከታተላሉ የተባሉ ሰዎች ዲሾቻቸው ከተነቃቀሉ በሁዋላ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።

የሞባል ኢንተርኔት የስልክ አገልግሎትን ሙሉ በሙሉ የዘጋው ገዢው ፓርቲ፣ በዲሽ ከውጭ አገር የሚተላለፉ ስርጭቶችን በማፈን ህዝባዊ ተቃውሞውን ለማፈን ሙከራ እያደረገ ነው። የጀርመን መሪ አንጌላ መርክል ገዢው ፓርቲ ሚዲያውን ክፍት በማድረግ የዲሞክራሲ ተቋማት እንዲጠናከሩ እንዲያደርግ ባሳሰቡ ማግስት የሚዲያ አፈናው ተጠናከሮ ቀጥሎአል።

ገዢው ፓርቲ የውጭ የመገናኛ ብዙሃን ህዝባዊ ንቅናቄውን እንዲጀመር አድርገዋል በማለት ወቀሳ እያቀረበ ነው።