በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ እየከፋ መምጣቱን የአውሮፓ ኅብረት አወገዘ

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :-የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ  የሰብአዊ መብት እና የልማት ኮሚቴ ዛሬ ባከሄደው መደበኛ ስብሰባ በኢትዮጵያ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ አትኩሮት ሰጥቶ ተወያይቷል ፡፡ በኢትዮጵያ በተካሄደው ህዝባዊ አመፅ ስለተገደሉት ንፁሀን የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች እንዲሁም ባለፈው እሁድ በመላው ኢትዮጵያ ለተከታታይ ስድስት ወራት የሚቆየውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስመልክቶ ውይይት ተካሂዷል። በዚህ ስብሰባ ላይ የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ኤክስፐርቶች፣ የኅብረቱ የውጪ ድጋፍ አገልግሎት ባለሞያዎች እና የኢትዮጵያ ኢምባሲ ተወካዮች በስፍራው ተገኝተዋል።

በዚህ ስብሰባ ላይ የተገኙት የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የሰብአዊ መብት እና የልማት ኮሚቴ አባላት በኢትዮጵያ ያለው ህገወጥ እስር፣ ግድያ እና እምቢተኝነቱን ተቋውሞ ተከትሎ በመንግስት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዳሳሰባቸው እና በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብት አያያዝ ወደ ከፋ ደረጃ ላይ የሚወስደው ስለመሆኑ በስብሰባው ላይ ለተገኙት ህብረት ኮሚሽን ኤክስፐርቶች፣ የአውሮፓ ህብረት የውጪ ድጋፍ አገልግሎት ባለሞያዎች እና ለኤንባሲው ተወካዮች ተናግረዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የሰብአዊ መብት እና የልማት ኮሚቴ አባላት እና የአውሮፓ ህብረት የውጪ ድጋፍ አገልግሎት ባለሞያዎች ህብረቱ በኢትዮጵያ ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር እና የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት አያያዝን  በተመለከተ አትኩሮት በመስጠት ቅድሚያ እንዲሰጥ  አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪም የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ  የሰብአዊ መብትና የልማት ኮሚቴ በበኩሉ ዛሬ ባከሄደው መደበኛ ስብሰባ በኢትዮጵያ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ አጽኖት በመስጠት የኢትዮጵያ መንግስት ካለምንም ቅድመሁኔታዎች የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ቅድሚያ በመስጠት የሰብአዊ መብት አያያዝን እንዲያሻሽል  መወያየቱን ኢሮፒያን ፓርላሜንት ኒውስ ዘግቧል።