ጥቅምት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአርማጭሆ ወረዳ በቅርቡ ከአገዛዙ ታጣቂዎች የሚደርስባቸውን ጥቃት በመሸሽ ራሳቸውን ያደራጁ የክልሉ ነዋሪዎች ትናንት ሁለት የፌደራል ፖሊሶችን ጭኖ በሚሄድ አንድ መኪና ላይ በፈጸሙት ጥቃት አንደኛው ሲገደል ሌላው ፖሊስ ቆስሏል።
በጠገዴ ደግሞ የመንገድ ስራ ለማስጀመር ወደ አካባቢው በተንቀሳቀሱ ባለስልጣናት ላይ ለመውሰድ የታሰበው እቅድ ባለስልጣናቱ መንገድ ቀይረው በመጓዛቸው ሳይሳካለቸው መቅረቱን የገለጹት እነዙህ ሃይሎች፣ ይሁን እንጅ የገዢው ፓርቲ ንብረት የሆነ አንድ መኪና ሲያልፍ በጥይት መመታቱን ገልጸጠዋል።
በአካባቢው የሚንቀሳቀሱት ሃይሎች ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ሲፈጽሙ የቆዩ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰአት የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት በወታደራዊ አጀብ ካልሆነ በስተቀር ወደ አካባቢው መንቀሳቀስ አቁመዋል።