የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ስብሰባቸውን ጀመሩ

መስከረም ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- 36ቱ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላቱ  በክልሉ ፕ/ት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ላይ ጠንካራ አስተያየቶችን እየሰጡ ነው። አቶ ገዱ አንዳርጋቸውም ክልሉን በደንብ አልመራነውም ልንለቅ ይገባል በማለት ሁሉም አባላት ተጠያቂዎች መሆናቸውን ገልጿል። አቶ ገዱ ብአዴን ለክልሉ ያመጣው ልማት የለም፣ ተገኘ የተባለውም ለውጥ ዘመን ያመጣው ነው ብለዋል ።