መስከረም ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገዥውን የህወሃት ኢህአዴግ መንግስት በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ዝግጅት በማድረግ ላይ እያሉ እሁድ ምሽት ላይ መያዛቸውን የከተማዋ የፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ጃፖት ኮሜ አስታውቀዋል። ኮማንደሩ አክለውም ያልተፈቀደ ስብሰባ በማድረጋቸው ክስ እንደሚቀርብባቸውም አሳስበዋል። ከተያዙት ኢትዮጵያዊያን ውስጥ የተወሰኑት ማንነታቸውን የሚገልጽ ሕጋዊ መረጃ ሳይዙ ካለ ፍቃድ በሕገወጥ መንገድ ድንበር ጥሰው የገቡ መሆናቸውንና ከፍርድ ውሳኔው በኋላ ወደ አገራቸው ሊላኩ ይችላሉም ብለዋል።
ተሰብሳዊዎቹ በኢሬቻ በዓል ላይ በንጹን ዜጎች ላይ ከደረሰው እልቂት ከሰዓታት በኋላ መሰባሰባቸውን ፖሊስ ገልጾ በኢትዮጵያ ያለው ሕዝባዊ ተቃውሞ ከመሬት ጉዳይ አልፎ መንግስት እንዲቀየር የሚፈልጉ የተቃውሞ ሰልፎች እየተበራከቱ መምጣታቸውን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል።