መስከረም ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምዕራብ ጎጃም ዞን በጢስ አባይ ከተማ አንድ ፖሊስ በእስር ላይ የነበረን ወጣት በህዝብ ትራንስፖርት ወደ ባህርዳር በመውሰድ ላይ እያለ ሁለት ወጣቶች ወደ አውቶቢሱ በመግባት ከከተማዋ ወጣ እንዳሉ ፣ ፖሊሱን በጩቤ በመውጋት ገድለው እስረኛውን እና የፖሊሱን የጦር መሳሪያ ይዘው ማምለጣቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል።
ጥቃቱን ያደረሱትን ሰዎች ለመያዝ በርካታ ወታደሮች ወደ አካባቢው ተሰማርተው ህዝቡን እያሰቃዩት መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ጥቃቱን ያደረሱት ሰዎች የልጁ ጓደኞች መሆናቸው ቢታወቅም፣ ወጣቱ በምን ጉዳይ እንደታሰረ ግን ለማወቅ አልተቻለም።