መስከረም ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በወልቂጤ፣ በቸሀ እና በእንድብር ካለፉት ሶስት ቀናት ወዲህ በግድግዳዎችና በዛፎች ላይ የተቃውሞ ጽሁፎች ተለጥፈው ይታያሉ።
በየከተሞቹ አደባባይ ላይ ተለጥፈው ከሚታዩት ጽሁፎች መካከል ፦”ዶክተር ብርሃኑ ነጋ የነጻነት ታጋይ እንጂ አሸባሪ አይደለም!፣ የአማራና የኦሮሞ ህዝብ ያነሳው ጥያቄ የኛም ጥያቄ ነው! በአማራና በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው ድርጊት እኛንም አሞናል! ጉራጌ ከመርካቶ፣ ከአትክልት ተራ፣ከ እፎይታ ተፈናቅሎ ምን የጠብቃል?” የሚሉት ይገኙበታል።