በባህር ዳር ከተማ ድባንቄ መድሃኒ አለም በመባል በሚታወቀው የቀብር ቦታ ሌሊት ሌሊት ያልታወቁ ሰዎች እንደሚቀበሩ የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ተናገሩ፡፡

መስከረም ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- የሃይማኖቱ አባቶች እንደሚሉት  በየቀኑ ከሶስት እስከ አምስት የሚደርሱ አስክሬኖችን የመንግስት ወታደሮች ማንም በማያይበት  ሰዓት አምጥተው የቀብራሉ፡፡

አባቶቹ  በሌሊት ማህሌት ለማድረስ በሚንቀሳቀሱበት ሰዓት ከባህር ዳሩ መኮድ የጦር ካምፕ አካባቢ በሚመጡ ፒክ አፕ መኪናዎች ተጭነው የሚመጡ አስክሬኖች እንደሚቀበሩ የሚገልጹት ምንጮች፣ ባህርዳርን ጨምሮ ከተለያዩ የአማራ ከተሞች በሰላማዊ ሰልፍ ተሳትፋችኋል በሚል የሚታፈሱት ወጣቶች አስከሬን ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬያቸውን ተናግረዋል፡፡

ወጣቶቹ  በተለይ ቤንሻንጉል ጉሙዝ በሚገኝ ጫካ ውስጥና በብር ሸለቆ የጦር ማሰልጠኛ ካምፕ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ተሰቃይተው ሲደክሙ ባህር ዳር ወደ ሚገኘው የመኮድ ወታደራዊ ሆስፒታል አምጥተው ህክምና እንደሚያደርጉላቸውና ከአቅምበላይ የተደበደቡት ህይወታቸው በሚያልፍበት ጊዜ በባህር ዳር መድሃኔያለም ቤተ ክርስቲያን በድብቅ እንደሚቀበሩ ጉዳዩን በቅርብ የሚያዉቁ ሰዎች ይናገራሉ።