መስከረም ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ርእሰ መስተዳድርና የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ሙክታር ከድርና ምክትላቸው ወይዘሮ አስቴር ማሞ ከሥልጣውናቸው የተነሱት የኦህዴድ ማዕከላቅዊ ኮሚቴ ከመስከረም 04 ቀን 2009 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ለስድስት ቀናት ባካሄደው ግምገማ ላይ ነው።
በምትካቸውም አቶ ለማ መገርሳ የድርጅቱ ሊቀመንበር እና ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።
የመንግስት ሚዲያዎች አቶ ሙክታር ከድርና ወይዘሮ አሳቴር ማሞ በፈቃዳቸው እንደለቀቁ ቢዘግቡም፤ የውስጥ ምንጮች ግን በኦሮሚያ ክልል ከተቀሰቀሰው አመጽ ጋር ተያይዞ መገምገማቸውንና ከሥልጣን እንዲነሱ መደረጋቸውን ተናግረዋል። ከቀራት በፊት እንዲሁ ከኦሮሚያ ክልሉ አመጽ ጋር ተያይዞ ከሳልጣን የተነሱት አቶ ዘላለም ንጀማነህ ለ እስር መዳረጋቸው ይታወቃል።
አቶ ወርቅነህ ገበዬሁ በደህነት ሹሙ በአቶ ጌታቸው አሰፋ በሚመራው የደህንነት ቡድን ውስጥ የሰሩ፣ቀጥሎም በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነርነት ያገለፈሉና አሁን የኦሮሚያ ክልል ሹም ሆነው ስልጣን እስኪረከቡ ደረስ በትራንፖርትና መገናኛ ሚኒስትርነት ሲሰሩ ቆይተዋል።
አዲሶቹ ተሿሚዎች ከደህንነትና ከፖሊስ ክፍሉ ጋር የተያያዘ ታሪክ ያላቸው መሆናቸው፤ ሹመቱ ህወኃት የኦሮሚያን ህዝባዊ አመጽ ለማፈን ካለው ፍላጎት ጋር የተያያዘ ነው የሚል ትችት አስከትሎበታል።