በስፔንና ደቡብ ኮሪያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍና የሻማ ማብራት ሰነስርዓት አካሄዱ

ኢሳት (መስከረም 10 ፥ 2009)

ነዋሪነታቸው በስፔን እና ደቡብ ኮሪያ መዲና ሴ’ኦል ከተማ የሆነ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ መንግስት በመፈጸም ላይ ያሉ ግድያዎችን በማውገዝ በሀገሪቱ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍና የሻማ ማብራት ሰነስርዓት ማካሄዳቸው ከሃገራቱ ለኢሳት የደረሱ መርጃዎች አመልክተዋል።

በስፔን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደብዳቤን በማስገባት ያላቸውን ተቃውሞ ያቀረቡ ሲሆን፣ የሃገሪቱ መንግስትም ያቀረቡትን ተቃውሞ ልዩ ትኩረት በመስጠት እንዲከታተላቸው አሳስበዋል።