መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ተካሂዶ በነበረው ተቃውሞ ላይ ተሳትፈሃል በሚል የተያዘው ፍጹም የተባለው ወጣት ሸዋ ሮቢት እስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ ድብደባ እና ስቃይ ተፈጽሞበት ህይወቱ ካለፈ በሁዋላ አስከሬኑን ወደ ቂሊንጦ በማምጣት በእሳት እንደተቃጠለ ተደርጎ ለቤተሰቦቹ መሰጠቱን ምንጮች ገልጸዋል።
የፍጹም የቀብር ስነስርዓት ትናንት በቦሌ ሚካኤል ተፈጽሟል።