በኮንሶ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ወታደሮች በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጥቃት ፈጸሙ

መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- ከኮንሶ የዞን አስተዳደር ጋር በተያያዘ  ካለፉት 2 አመታት ጀምሮ ሲንከባለል የቆየው ጥያቄ፣ ወደ ደም አፋሳሽ ግጭት እያመራ ሲሆን፣

ግጭቱ ዛሬ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ በርካታ ሰዎች ህይወታቸው አልፎአል። የቆሰሉና ቤቶቻቸው የተቃጠሉባቸው ሰዎች መኖራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አንድ ቤታቸው የተቃጠለባቸው ሰው እንደገለጹት ዛሬ ብቻ ሁለት መንደሮች እንዲቃጠሉ መደረጉንና ተጨማሪ አደጋ ይደርሳል ብለው እንደሚሰጉ ገልጸዋል።

ጥያቄያችን ሰላማዊ የነበረ ቢሆንም፣ እነሱ ግን ሃይል አደራጅተው ጥቃት ፈጸሙብን ሲሉ እኝሁ ነዋሪ ገልጸዋል ።

ሌላው የአካባቢው ነዋሪ እንደሚሉት ደግሞ ወታደሮቹና የልዩ ሃይል አባላት በአጎራባች ወረዳዎች የሚገኙ ብሄረሰቦችን በኮንሶ ላይ እንዲነሱ በማድረግና ፊት ሆነው በመምራት የብሄርሰብ

ግጭት እንዲነሳ ለማድረግ እየሞከረ ነው። የጦር መሳሪያ በታጠቁ የአካባባው ነዋሪዎችና በወታደሮች መካከል የተኩስ ልውውጥ መደረጉን ተከትሎ፣ ወታደሮች ከባድ መሳሪያዎችን ሳይቀር

መጠቀማቸውንም ግለሰቡ ተናግረዋል። በሶስት ቀበሌዎች የሚገኙ ቤቶች እንዲሁም የእርሻ ማሳዎችም ተቃጥለዋል።

የኮንሶ ህዝብ ከሰገን ዞን ወጥቶ ራሱን ችሎ እንዲተዳደር ጥያቄውን እስከጠቅላይ ሚኒስትሩ ድረስ ቢያቀርብም ፣ አጥጋቢ መልስ ማግኘት አልቻለም። የመንግስት ስራና ትምህርት ቤቶች ከተዘጉ

በርካታ ወራቶች ተቆርጠዋል። የአገር ሽማግሌዎችና ወጣቶችም እንዲሁ እየታደኑ ታስረዋል።