ኢሳት (መስከረም 2 ፥ 2009)
የዘንድሮውን የኢድ አል አድሃ በዓል ለማክበር በጎንደር ከተማ የተሰባሰቡ የሙስሊሙ ማህበረሰብ በከተማዋ ባለስልጣናት ባለኮከብ ባንዲራን ይዘው እንደወጡ የተሰጣቸውን መልዕክት ሳይቀበሉ መቅረታቸው ታውቋል።
ለበዓሉ አከባበር የታደሙት የሙስሊሙ ማህበረሰብ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ወደጎን በመተው በዕለቱ የተቃውሞ መልዕክት ነው ያሉትን ቀይ ፊኛ ወደሰማይ ሲለቁ የሚያሳይ ቪዲዮ መልዕክት ለዜና ክፍላችን ደርሷል።
ቀይ ፊኛን ወደ ሰማይ መመልቀቁ ጎን ለጎን ታዳሚዎች እጃቸውን በማጣመር በሃገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈጸሙ ግድያዎችን ሲያወግዙ ማርፈዳቸውንም ከሃገር ቤት ከደረሰን መረጃ ለመረዳት ተችሏል።