በዛንቢያ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በመኪና አደጋ ሞቱ

ጳጉሜ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዛንቢያ አድርገው ወደ ደቡብ አፍሪካ በማቅናት ላይ እያሉ የመኪና አደጋ ካጋጠማቸው ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ውስጥ ሁለቱ በደጋው ወዲያውኑ

ሕይወታቸውን አጥተዋል። ከአደጋው የተረፍት 12ስደተኞች በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይኦኤም እርዳታ ወደ ዋናከተማዋ ሉሳካ ተወስደዋል።

የሁለቱ ሟች ኢትዮጵያዊያን አስከሬን እስካሁን ድረስ በሚንባላ ጄኔራል ሆስፒታል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የዛንቢያ ስደተኞች ጉዳይ ከአይኦኤም ጋር በመተባበር

አስከሬናቸውን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ጥረት እየተደረገ  ነው።

በተጨማሪም በሕገወጥ አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ወደ ዛንቢያ ከገቡ 38 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ውስጥ ሃሙስ እለት 19 የሚሆኑት ምንነቱ ባልታወቀ አደጋ

ሕይወታቸውን ማጣታቸውን አይኦኤምአስታውቋል። ዛንቢያ ውስጥ በእስር ላይ ከሚገኙት 76 ስደተኞች ውስጥ 38 የሚሆኑት ከአደጋ የተረፉ ኢትዮጵያዊያን

ስደተኞች በመጀመሪያው ዙር ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን ሉሳካ ታይምስአክሎ ዘግቧል።

በተጠናቀቀው 208 ዓ.ም አያሌ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በስደት ላይ በሚያጋጥማቸው አደጋ ሕይወታቸውን አጥተዋል። በሽዎች የሚቆጠሩት ወጣቶች አስታዋሽ

በማጣት በተለያዩ አገራት በእስር ቤት ውስጥ እየማቀቁ ነው።