በደቡብ ጎንደር እብናት ከተማ ሕዝቡ የራሱን አስተዳደር መሰረተ

ነሃሴ  ( ) ቀን ፳፻፰ / ኢሳት ዜና :-እየተቀጣጠለ የመጣው ሕዝባዊ እቢተኝነት አድማሱን በማስፋት በእብናት እና አርባያ ከተሞች ጨምሮ በአጎራባች የገጠር ገበሬ ማኅበራት ሕዝቡ የጎበዝ አለቃዎች በመምረጥ የራሱን አስተዳደር መስርቷል።

የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ወጣቶች ራሳቸውን በማደራጀት ከተማዋን ተቆጣጥረው አስተዳዳሪዎቻቸውን ከመምረጣቸውም በተጨማሪ በግፍ የታሰሩ ወጣቶችን  አስፈትተዋል።

በከተማዋ ምንም ዓይነት የንግድ እንቅስቃሴ የሌለ ሲሆን የመንግስት ቢሮዎችን ጨምሮ የግል ድርጅቶች ዝግ ሆነው ሕዝቡ በቤት ውስጥ ተቀምጧል።

ከዚህም ሌላ  አቅም ለሌላቸው ዜጎችና የጎዳና ተዳዳሪዎች ገንዘብ በማዋጣት ነጋዴዎችና ወጣቶች አስተዋጾ እያደረጉ እንደሆነ ተገልጻል።

ወጣቶቹ እብናትን ከሌሎች ከተማዎች የሚያገናኙ አውራ ጎዳናዎችን በመዝጋት እራሳቸውን ከጥቃት በመከላከል ላይ ናቸው።

የገዥው ፓርቲ ታጣቂዎች ሙሉ ለሙሉ ከከተማዋ ተጠራርገው የወጡ ሲሆን፤  ሕዝቡ ካሁን በኋላ በህወሃት ኢህአዴግ አስተዳደር አንገዛም ሲል የአቋም መግለጫ ማውጣቱም ታውቋል።