በቦዲ አርብቶአደሮች መንገድ በመዝጋታቸው የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች መንቀሳቀስ አልቻሉም

ነሃሴ  ( ሃያ ስድስ ) ቀን ፳፻፰ / ኢሳት ዜና :- በደቡብ ክልል  የቦዲና ሙርሲ ጎሳዎች መሬታቸውን ለሸንኮራ አገዳ ተክል መወሰዱን ተከትሎ የጀመሩትን ተቃውሞ በመቀጠል መንገዶችን በድንጋይና በእንጨት በመዝጋት ተቃውሞአቸውን እየገለጹ ነው።

አንድ የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካ ሹፌር የቦዲ ማህበርሰብ አባል  ገጭቶ መግደሉን ተከትሎ የማህበረሰቡ አባላት ለሟች ቤተሰብ ካሳ ለመሬታችንም ተገቢው ክፍያ ይከፈለን በማለት በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ሰሚ አላገኙም። አርብቶአደሮቹ በዚህ በመበሳጨት መንገዶችን በመዝጋት ታቃውሞአቸውን እየገለጹ ሲሆን፣ የስኳር ፋብሪካውን ለመጎብኘት የሄዱ ከ40 በላይ እንግዶች መመለሻ አጥተው ተቸግረዋል። ጎብኝዎቹ እና የፋብሪካው ሰራተኞች ለአመት በአል ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመሄድ ቢፈልጉም ፣ መጓዝ አልቻሉም።