የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በዜጎች ላይ የሚደረገው የኃይል እርምጃዎች እንዲቆሙ ሲል ጠየቀ

ነሃሴ  ( ሃያ ስድስ ) ቀን ፳፻፰ / ኢሳት ዜና :- በመላው ኢትዮጵያ በመንግስት ታጣቂዎች የሚፈጸሙ አላስፈላጊ የኃይል እርምጃዎች ካለምንም ቅድመ ሁኔታዎች እንዲቆሙ ሲል ሰመጉ ሪፖርት አድርጓል። ሰመጉ ዜጎችን ከመኖሪያቸው ማፈናቀል፣ግድያ፣ እስራትና በሕገመንግስቱ እና በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች የተፈቀዱ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቶች እንዲከበሩ ጠይቋል። አላግባብ ከሕግ ውጪ ንጹሃንን የገደሉ በሕግ እንዲጠየቁና ጉዳተኞች ካሳ እንዲሰጣቸው ሲል ሰመጉ አሳስቧል።የጸጥታ ኃይሎች ካለምንም ተጠያቂነት በተለያዩ የአገርቱ አካባቢዎች የሚወሰዱዋቸው እርምጃዎች ግድያዎችና፣ የአካል ማጉደል ከማድረሳቸው በተጨማሪ ለሰላምና መረጋጋት ጠንቅ እየሆኑ ነው ብሏል ሰመጉ። በወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄን በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ላይ ግድያ፣የጅምላ እስራትና ድብደባ መፈፀሙን ሰመጉ በመረጃ አረጋግጧል። በባርዳር ከተማም በተመሳሳይ ከ50 በላይ ንጹሃን ዜጎች በታጣቂዎች መገደላቸውን፣ መደብደባቸውንና ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ በገፍ መታሰራቸውን ሰመጉ አስታውቋል። በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ክልልም በተለያዩ ከተሞች ግድያ፣ እስራትና ድብደባ አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል። በዜጎች መሃከል የብሄር ግጭት እንዲነሳ ሆን ተብሎ በገዥው መንግስት እየተሞከረ መሆኑን ሰመጉ በሪፖርቱ አመላክቷል።

በዛሬው እለት በፊንላንድ ሔልሲንኪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንበሀገራችን ላይ እየተካሔደ ያለውን የጅምላ እስራትና ግድያ

በመቃወም ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍአካሒደዋል።

ሰልፈኞቹም በሰልፉ ላይ ፊንላንድ እና የአውሮፓ ህብረት በህወሀት አገዛዝ ላይ የሚከተሉትን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እንዲቀይሩ ፣ እንዲሁም በህዝባችን

ላይ እየተካሔደ ያለውን ማሰቃይት፣ እስር እና ግድያ በይፋ እንዲያወግዙ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንየጠየቀውን

የአለም አቀፍ ገለልተኛ አካል ምርመራ እንዲደግፉ ጠይቀዋል።

ሰልፈኞቹ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች እየተካሔደ ላለው ፀረ ህወሀት ትግል አጋርነታቸውን ገልፀው ወደፊትም ሁለንተናዊ  ድጋፍ እንደሚያደርጉ

አረጋግጠዋል።

በሰልፉም ላይ የፊኒሽ  ኦሮሞ ማህበር ፣ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ፣ የኦጋዴን ኮሚኒቲ እና የኮንሶ ኮሚኒቲ አባላት ተገኝተዋል።

ከፊንላንድ የወጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናት  እና የፓርላማ ተወካዮች ጋር ሰፊ ውይይት ተካሒዷል።