ኢሳት (ነሃሴ 6 ፥ 2008)
የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በባህር ዳር ከተማ በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች የጅምላ እስር በማካሄድ ላይ መሆናቸውን ነዋሪዎች ለኢሳት አስታውቀዋል።
በከተማዋ አዳዲስ እስር ቤቶች መከፈታቸውን የተናገሩት እማኞች ተቃውሞውን ተከትሎ በተለይ ወጣት የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ለእስር መዳረጋቸውን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ገልጸዋል።
ይሁንና የጸጥታ ሃይሎች እየወሰዱ ያለውን የዕስር ዘመቻ ተከትሎ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ለእስር የተዳረጉ ሰዎች እንዲፈቱ በመጠየቅ ላይ ሲሆኑ ከተማዋ በበርካታ የጸጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ስር መሆኗን ለመረዳት ተችሏል።
በሰሜን ጎንደር ዞን ስር በሚገኙ በርካታ ወረዳዎች የመንግስት መዋቅሮች አገልግሎት መስጠት ማቆማቸውንና ነዋሪዎች ዳግም ተቃውሞ ማቅረብ መጀመራቸውን ሃሙስ ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ መዘገባችን ይታወሳል።