ኢሳት (ሃምሌ 8 ፥ 2008)
በደቡብ ሱዳን ባለፈዉ ሳምንት ያገረሸዉን ግጭት ተከትሎ ሐገራት ዜጎቻቸውን ማዉጣት ጀመሩ። ሆኖም ኢትዮጵያዉንን የማዉጣት እንቅስቃሴ ባለመጀመሩ ለአደጋ መጋለጣቸዉን ጁባ የሚገኙ ኢትዮጵያውን ለኢሳት ገልፀዋል ።
የደቡብ ሱዳን የነፃነት በዓል በሚከበርበት ወቅት ያገረሸው ግጭት እየተስፋፋ መሄድን ተከትሎ አሜሪካና የአዉሮፓ ሀገራት ዜጎቻቸዉን ማዉጣት የጀመሩ ሲሆን ፣ ኬንያና ኡጋንዳ በተመሳሳይ ዜጎቻቸዉን በማጓጓዝ ላይ መሆናቸዉን መረዳት ትችሏል።
በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያዉንን ለማዉጣት ግን እንቅስቃሴ ባልመጀመሩ፣ ኢትዮጵያውያኑ ስጋት ላይ ወድቀዋል። ግጭቱን ተከትሎ ህግና ሥርዓት እየፈራረሰ በመምጣቱ ዘረፋ ተስፋፍቷል። በዚህ ስጋት የገባቸው ኢትዮጵያውን መንግስት እንዲያወጣቸዉ ፣ ወይንም ባለበት ከለላ የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲመቻችላቸዉ ጁባ ባለዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል ጥያቄ አቅርበዋል ፣ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በኤምባሲዉ በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም። ኢትዮጵያውንኑ ለማዉጣትም እንቅስቃሴ አልታየም።
ዩስ አሜሪካ ከስራ ጋር በተያያዘ የሚቀሩ ሠራተኞችን ለመጠበቅ 47 ወታደሮችን ወደ ደቡብ ሱዳን መላኳን ፐሬዝዳንት ባራክ ኦባማ አስታውቀዋል። ተጨማሪ 130 ወታደሮች ለተጠባባቂነት ወደ ጁቡቲ ተልከዋል።
በደቡብ ሱዳን የተቀሰቀሰዉ ግጭት ኢትዮጵያ ፣ ኬንያና፣ ሩዋንዳ በወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ለመፍታት እየተዘጋጀች መሆናቸዉን ይፋ ሆኗል።