ሐምሌ ፮ ( ስድስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአርሲ ዞን የጢዮ አካባቢ ነዋሪዎች ማዳበሪያ ጭነው በአካባቢው የሚያልፉ የጭነት መኪናዎችን በማስቆም ማዳበሪያው እኛን አልፎ ወደሌላ አካባቢ ከመሄዱ በፊት ለኛ ሊሰጠን ይገባል በማለት ተቃውሞ ማሰማታቸው ታውቋል።
በሌላ በኩል በምዕራብ አርሲ በአዳባ ተቃውሞ ምክንያት ከፍተኛ ድብደባና እንግልት የደረሰባቸው ሀጂ ጉዬ ዱላ የተባሉ ትልቅ የሀይማኖት አባት ህይወታቸው አልፏል።
በተቃውሞው ወቅት በወጣቶችና በፖሊሶች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ለማብረድ ሙከራ ሲያደርጉ በደረሰባቸው ጉዳት ሆዳቸው ላይ ለእብጠት የተዳረጉት ሀጂ ጉዬ፣ በመጀመሪያ ጥቁር አንበሳ ከዚያም በአሰላ ሆስፒታል ለወራት የህክምና ክትትል ሲያደርጉ ቢያደርጉም ጉዳታቸው ከፍ ያለ ስለነበር ከትናንት በስቲያ አርፈዋል። የሃጂጉዬ የቀብር ስነስርዓት ዛሬ በምእራብ አርሲ በትውልድ አካባቢያቸው የተፈጸመ ሲሆን
በስፍራው የተገኘው በርካታ ህዝብ ተቃውሞ አሰምቷል ።