ሰኔ ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአገሪቱ ወታደራዊ አዛዥ ጄኔራል ካቱምባ ዋማላ በሶማሊያ ያለው ሁኔታ መሻሻል አላሳየም በሚል ሰራዊታቸውን በታህሳስ ወር እንደሚያስወጡ ገልጸዋል። የሶማሊያ ወታደሮች የአገሪቱን ጸጥታ ይቆጣጠራሉ ተብሎ ቢጠበቅም፣ አለመሳካቱን ጄኔራሉ ገልጸዋል።
ለሶማሊያ ወታደሮች ስልጠና የሚሰጡት አሜሪካ፣ እንግሊዝና ቱርክ ስራቸውን በቅንጅት አይሰሩም በማለት ጄኔራሉ ትችት ያቀረቡ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በአገሪቱ በሰላም አስከባሪ ስም የተሰማሩት ሃይሎች በቅንጅት እንደማይሰሩ ተናግረዋል። ኢትዮጵያን ጨምሮ ጦራቸውን ወደ ሶማሊያ የላኩ የምስራቅ አፍሪካ አገራት ከአልሸባብ በየጊዜው በሚደርስባቸው ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻቸውን አጥተዋል።