የኢትዮጵያ  የስኳር  ፋብሪካ  ፕሮጀክቶች  በእዳ  መዘፈቃቸውንና  በአገሪቱ  ምጣኔ  ሃብት ላይ ስጋት መደቀናቸውን ጥናቶች አረጋገጡ

ሰኔ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-

በገዥው ፓርቲ ተነድፈው ኢትዮጵያን በዓለም አስረኛ ስኳር ላኪ ያደርጓታል ተብለው የተጀመሩት የስኳር ፕሮጀክቶች ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት በእዳ

መዘፈቃቸውን ጥናቶች አጋልጠዋል።

ለፕሮጀክቶቹ መስተጓጎል የባለሙያዎች እጥረትና  የፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ፈንድ ማጣት በዋነኛነት የተጠቀሱ ችግሮች መሆናቸው በጥናቱ ተመልክቷል።

በደቡብ ክልል በኦሞ ሸለቆ ውስጥ ለሚገኘው የኩራዝ ስኳር ፋብሪካ መስተጓጎል ዓይነተኛ ችግሮቹ ፦አካባቢው ለልማት ምቹ የሆነ ስፍራ ላይ አለመገኘቱና የጥሬ

እቃ አቅርቦት እጥረት ሲሆኑ፤ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ድርጅት ሜቴክ የፈጠረው ችግርም  የፕሮጀክቱን ቀጣይ ትርፋማነትስጋት ውስጥ ጥሎታል ተብሏል።

በኬኒያ ቱርካና ሃይቅ ብዝኅሕይወት ላይም አደጋ ከመደቀኑ በተጨማሪ በታችኛው የኦሞ ሸለቆ  ድንበር አቅራቢያ በሚኖሩ ከ200 ሽህ በላይ  አርብቶ አደሮች

ህልውና ላይ ስጋት

መጋረጡን የኦሞ ቱርካና የጥናት ማእከል ተመራማሪ የሆኑት ቤኔዴክት ባምስኪ በጥታናታዊ ሪፓርታቸውአስታውቀዋል።

4.6 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ተደርጎባቸው እ.ኤ.አ. በ2011 የተጀመሩትና በመንግስት ባለቤትነት የሚተዳደሩት በመላው አገሪቷ ውስጥ የሚገኙ

10 የስኳር ፋብሪካዎች በአምስት

ዓመታት ውስጥ 2.3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ስኳር ያመርታሉ ተብሎ ተብሎ የነበረ ቢሆንም እስካሁንድረስ ግን የትኞቹም በአግባቡ ስራቸውን አልጀመሩመ።

ዓለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት በምሕጻረቃሉ አይኤምኤፍ ባወጣው ሪፖርት በዘንድሮው ዓመት የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት እድገት ከነበረበት 8.7 % ወደ 4.5% እንደሚያሽቆለቁል  አስታውቋል።በጋምቤላ ክልል ውስጥ የ100 ሽህ ሄክታር ባለይዞታ እንደነበረውና በህንዳዊው ባለሃብት ሲንቀሳቀስ

እንደቆየው እንደ ካራቱሪ ግሎባል

ሊሚትድ ያሉ  በመንግስት የቀረቡት የግብርና ኢንቨስትመንቶችም  ሙሉ ለሙሉ አዋጪ እንዳልሆኑና በኪሳራ መደምደማቸውን ጥናቱ አረጋግጧል።

ከቻይናው ኢምፓርትና ኤክስፓርት ዴቨለፕመንት ባንክና ከቻይና ንግድና ኢንዱስትሪ ባንኮች  1.63 ቢሊዮን ዶላር ብድር መገኘቱን የኢትዮጵያ

ፋይናንስ ሚንስቴር አስታውቋል።

የመጀመሪያው ዙር  የእዳ ክፍያ የሚጀመረው  በመጪው ጥቅምት ወር መሆኑን የብድር ስምምነቱ ሰነድ ውል ላይ ሰፍሯል።

በተጨማሪም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 49 ቢሊዮን ብር ማለትም 2.25 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ብድር በፕሮጀክቱ ስም ተወስዷል። ይህን ጉዳይ አስመልክቶ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ቃል አቀባይ አቶ ጋሻው አይችሉህም ተጠይቀው የፕሮጀክት ጥናቱ ሂደቱ ሳይጠናቀቅ ምላሽ ለመስጠትፈቃደኛ እንዳልሆኑ ተናግረዋል።

ነዋሪነታቸውን በለንደን ያደረጉት የምጣኔ ሃብት ተመራማሪ አቶ አብዱልመናን መሃመድ ሃምዛ 40% የሚሆነውን እዳ የተሸከመችን አገር ይዞ እንደዚህ ዓይነት

የፕሮጀክት ኪሳራ

ሲያጋጥም ትልቅ አገራዊ ክስረት ያስከትላል ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።  ከኩራዝ አንድ ስኳር ፋብሪካግንባታ እስካሁን ድረስ 75% ብቻ ስራውን ያጠናቀቀው

ሜቴክ ፤ፕሮጀክቱ ባልተጠናቀቀበት ሁኔታ 97% የሚሆነውን ቅድመ ክፍያ  መውሰዱን የብሉንበርግ ዘገባ ያመለክታል።