ኢሳት (ሰኔ 1 ፥ 2008)
የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መርማሪ ኮሚቴ በስደት የሚገኙ 500 ያህል ኤርትራውያን በማነጋገር ያጠናቀረው ይህ የኤርትራ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ሪፖርት፣ የግዳጅ ውትድርና፣ እስራት ግድያና ማሰቃየት በሃገሪቱ እንድሚፈጸም የሚዘረዝር ሲሆን፣ ኤርትራ ነጻነቷን ካገኘችበት እኤአ ከ1991 ጀምሮ የተከሰተው በሰው ልጆች ላይ የተፈጸመ ወንጀል በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንዲታይ የፀጥታው ም/ቤት እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ ያቀርባል።
በስዊዘርላንድ መዲና ጄኔቫ የወጣውን ኤርትራን የተመለከተውን ሪፖርት ተከትሎ የቢቢሲ ዘገባ ሜር ሃቻ አስመራ ላይ ያነጋገረቻቸው የምዕራብ ሃገራት ዲፕሎማቶች፣ ሪፖርቱ ተጨባጩን የኤርትራ ሁኔታ የማይገልፅና ገንቢ ያልሆነ ማለታቸው ተዘግቧል።
ኤርትራያውን በከፍተኛ ቁጥር ወደ አውሮፓ በመሰደድ ላይ መሆናቸውን በዚሁ ሪፖርት ያካተታቸው የብሪታኒያው ዜና ማሰራጫ ቢቢሲ ዘገባ፣ በ2015 አውሮፓ ገብተው ጥገኝነት ከጠየቁ ስደተኞች 25% በመቶ ኤርትራውያን መሆናቸውን አስፍሮ፣ በ 2011 659 ብቻ የነበረው የኤርትራ ጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር በ2015 38,971 መድረሱን ሪፖርቶችን መሰረት አድርጋ ዘግባለች።
ሆኖም አንድ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተንከባካቢ ተቋም ሰራተኞችን በመጥቀስ ሜሪ ሃፕ በሪፖርቷ እንዳካተተችው በኤርትራውያን ስም ጥገኝነት ከሚጠይቁት ውስጥ 30 በመቶ ያህሉ ኢትዮጵያውያን ና