ግንቦት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ድርጅት ( ኢሰመጉ) የአሁኑ የሰብአዊ መብቶች ድርጅት ( ሰመጉ) በ141ኛው ልዩ ሪፖርቱ በወልቃይት፣ በቅማንት፣ በቁጫና በኮንቶማ አካባቢዎች በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተገደሉ፣ የጠፉ፣ የታሰሩ እንዲሁም የተሰደዱ ሰዎችን እና በአጠቃላይ የደረሰባቸውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ይፋ አድርጓል።
ሰመጉ ከወልቃይት የአማራ ማንነት ጋር በተያያዘ የተገደሉ የ34 ሰዎችን ፣ ታፍነው የተወሰዱ የ47 ሰዎችን ፣ የታሰሩ የ 17 ሰዎችን እንዲሁም የተፈናቀሉ 137 ሰዎችን ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል። ከቅማንት ህዝብ ጋር በተያያዘ ደግሞ 22 ሰዎች መደላቸውን፣ 10 መቁሰላቸውን በስም ዘርዝሮ አቅርቧል። በቁጫ ከተነሳው የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ 42 ዜጎች አሁንም ድረስ በእስር ላይ እንደሚገኙ ገልጿል። ሰመጉ ያወጣውን ልዩ መግለቻ ሙሉውን እንደደረሰን እናቀርባለን።