ግንቦት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከግንቦት 1 ቀን 2008 ጀምሮ ፈቃዳቸው ከተሰረዘባቸው ድርጅቶች መካከል ከ 1997 ዓም ጀምሮ በስራ ላይ የነበሩ ይገኙበታል። እነዚህ ድርጅቶች ፈቃዳቸውን ለማሳደስ ፈቃደኛ ያልሆኑበት ምክንያት ምን እንደሆነ ቢሮው አልጠቀሰም።
ፈቃዳቸው ከተሰረዘባቸው ድርጅቶች አንዳንዶቹ ፈቃዳቸው የሀገር ውስጥ ስራና ሰራተኛን ማገናኘት ቢሆንም በገሀድ ወደአረብ አገራት ሰራተኞች የሚልኩ እንደነበሩና የውጪ ስራ ስምሪት መታገድ ጋር ተያይዞ በኪሳራ የተዘጉ መሆናቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች አስረድተዋል። የተቀሩት የመኖሪያ ቤት፣ የሆቴል ባለሙያዎች፣ ሞግዚቶች፣ የጥበቃ ሰራተኞችንና የመሳሰሉ በማቅረብ ስራ ላይ የተሰማሩ ነበሩ። ኤጀንሲው በአንድ ጊዜ 65 ያህል ፈቃድ ሲሰርዝ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ታውቆአል።