ወደ አገራችን አንመለስም ያሉ 27 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የርሃብ አድማ አደረጉ

ግንቦት ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሕገወጥ መንገድ ድንበር አቋርጣችሁ ወደ ኬንያ ገብታችኋል ተብለው በኢንቡ እስር ቤት ላለፉት ሃያ ሰባት ቀናት ታስረው የነበሩና የእስር ጊዜቸውን ያጠናቀቁ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የኬንያ መንግስት ወደ አገራቸው ሊመልሳቸው መወሰኑን በመቃወም የርሃብ አድማ አድርገዋል።
ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ምንም ዓይነት ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው በመሆኑ ኬንያ ውስጥ መቀመጥ አይችልም ሲል የአገሪቱ ፍርድ ቤት በይኗል። የኬኒያ የስደተኞች ጉዳይ በበኩሉ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተከትሎ ስደተኞቹን ወደ አገራቸው ለመላክ መወሰኑን ማስታወቁን ዘ ሲቲዚን ዘግቧል።