ኢሳት (ግንቦት 5 ፥ 2008)
ከቀናት በፊት በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ዛምቢያ ገብታችኋል ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉ 41 ሰደተኞች ኢትዮጵያዊያን በሶስት ወር እስራት ተቀጡ።
የሉአንግዋ ግዛት ፍርድ ቤት በስደተኞቹ ላይ የእስር ቅጣቱን ባስተላልፈ ጊዜ በየጊዜው ወደ ማላዊ የሚገቡ ኢትዮጵይዊያን ስደተኖች ቁጥር ለሀገሪቱ ስጋት እየሆነ መምጣቱን እንደገለጸም ሉሳካ ታይምስ ጋዜጣ አርብ ዘግቧል።
የእስር ቅጣት የተላለፈባቸው ስደተኞች ኢትዮጵያዊያኑ እድሜያቸው ከ 30 አመት በታች ሲሆን በዚምባብዌ በኩል ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናት እንደነበረ ታውቋል።
የ ሶስት ወር ቅጣት ከተላለፈባቸው 41 ዱ ኢትዮጵያዊያን በተጨማሪ ሰሞኑን በተመሳሳይ ድርጊት የተያዙ ከ 30 በላይ ኢትዮጵያዊያን ከቀናት በኋላ ለፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎም የጠበቃል።
የእስር ቅጣት የተላለፈባቸውን ስደተኛ ኢትዮጵያውያኑ እድሚያቸው ከ30 አመት በታች ሲሆን፣ በዛምቢያ የተገኙም በዚምባብዌ በኩል ወደ ደቡስ አፍሪካ ለማቅናት እንደነበር ታውቋል።
የሶስት ወር ቅጣት ከተላለፈባቸው 41ዱ ኢትዮጵያውያን በተጨማሪም ሰሞኑን በተመሳሳይ ድርጊት የተያዙ ከ30 በላይ ኢትዮጵያን ከቀናት በኋላ ለፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎም ይጠበቃል።
የእስር ቅጣት ከተላለፈባቸው መከከልም አንደኛው በነዋሪዎች ድብደባ ተፈጽሞበት በህክምና ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ሌላ አንድ ኢትዮጵያውያንም ለማምለጥ ሲሞክር ጉዳት ደርሶበታል ተብሎ በሆስፒታል እንደሚገኝ ሉሳካ ታይምስ ጋዜጣ በዘገባው አመልክቷል።
የሉአንግዋ ግዛት ፖሊስ ተጠሪ የሆኑት ረዳት ሱፐር ኢንቴንደንት ማታ’ኣ ሙሉታ ባለፈው ወርም 16 ኢትዮጵያውያን በተመሳሳይ መልኩ በቁጥጥር ስር ውለው እንደነበር ለመገናኛ ብዙሃን አስረድተዋል።
ይሁንና፣ ኢትዮጵያውያኑ መቼ ለፍርድ እንደሚቀርቡ ሃላፊው የሰጡት ዝርዝር መረጃ የሌለ ሲሆን፣ በሃገሪቱም በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙ ታውቋል።
በዛምቢያ ከሚገኙት ኢትዮጵያውያን በተጨማሪም በጎረቤት ማላዊ፣ ታንዛኒያ፣ ዚምባብዌና ሌሎች ሃገራትም በርካታ ስደተኞች በእስር ቤት እንደሚገኙ የተለያዩ አካላት ሲገልፁ ቆይተዋል።
በኢትዮጵያ ያለውን ፖለቲካዊ አለመረጋጋት በመሸሽ በየዕለቱ በርካታ ስደተኞች ከሃገር እየተሰደዱ እንደሆነም የአለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት መረጃ የመለክታል።