ኢሳት (ሚያዚያ 10 ፥ 2008
መቀመጫውን በአዲስ አበባ ያደረገው የአፍሪካ ህብረት በንጹሃን ዜጎች ላይ ጥቃትን የፈጸሙ አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡ ሰኞ ጥሪን አቅርቧል።
የግድያ ድርጊቱን ያወገዘው ህብረቱ የኢትዮጵያና የጎረቤት ደቡብ ሱዳን መንግስታት ያላቸውን ዘርፈ-ብዙ ስምምነት በመጠቀም ጥቃት የፈጸሙ አካላትን ለፍርድ እንዲቀርቡ አሳስቧል።
በዚሁ ጥቃት ታፍነው የተወሰዱ ኢትዮጵያውያንም በአስቸኳይ እንዲለቀቁ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ባወጣው መግለጫው የጠየቀ ሲሆን፣ መቀመጫቸውን በዚህ በአሜሪካና የተለያዩ ሃገራት ያደረጉ ኢትዮጵያውያንና ማህበራትም በግድያው የተሰማቸውን ሃዘን በመግለጽ ላይ ናቸው።