ሚያዚያ ፲(አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ የተከሰተው አስከፊ ርሃብ የዜጎችን ሕይወት አስጊ ሁኔታ ውስጥ ያስገባ ሲሆን በተለይ ሕጻናት ቀዳሚ የችግሩ ገፈት ቀማሽ መሆናቸውን ድርጅቱ ተገልጿል። በሃምሳ ዓመታት ውስጥ ተከስቶ የማያውቅ አደገኛ ችጋር በኢትዮጵያ ያንዣበበ ሲሆን ጉዳተኞችን ለመታደግ ከስድስት መቶ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ አፋጣኝ እርዳታ ከለገሽ አገሮች ይጠበቃል።
ዩኒሴፍ ሕጻናት በውሃ ጥምና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በፈጠሩባቸው የጤና መቃወስ ሳቢያ አስጊ ሁኔታ ውስጥ ስላሉ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ አፋጣኝ የነፍስ አድን እንዲያደርግ ድርጅቱ ጥሪውን አስተላልፏል።በምስራቅ አፍሪካ ከተከሰተው ድርቅ የኢትዮጵያ ከፍተኛውን የጉዳት መጠን እንዳስከተለ ዘኮሪያን ሄራልድ አክሎ ዘግቧል።