በድሬዳዋ ከተማ ከቤት ማፍረስ ጋር በተያያዘ ዜጎች ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸው ተገለጸ

ሚያዚያ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ በፌደራል ፖሊስ እና በከተማው ልዩ ፖሊስ ከፍተኛ ጥበቃ በሚካሄደው የቤት ማፍረስ ዘመቻ፣ በርካታ ነዋሪዎች ለችግር መዳረጋቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመልክቶአል፡፡
ከሚያዚያ 4 ቀን 2008 ዓም ጀምሮ በቀበሌ 02 ልዩ ስሙ ሳቢያን እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚካሄደው የቤት ፈረሳ ፣ እናቶች ፣ ኀጻናትና አሮጊቶች ሜዳ ላይ ወድቀዋል፡፡
ቤታቸው የሚፈርስባቸው ሰዎች ድርጊቱን ለመቃወም ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም፡፡ በተለይም በአሁኑ ወቅት ዝናብ ሌት ተቀን እየዘነበ በሚገኝበት ወቅት የቤት ፈረሳውን ማከናወን ሰብአዊነት የጎደለው ነው በማለት ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡