ኢሳት (የካቲት 29 ፥ 2008)
በነቀምቴ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ማቅረብ የጀመሩንት ጥያቄ ተከትሎ በዩኒቨርስቲው ትምህርት መቋረጡንና በርካታ ተማሪዎችም በጸጥታ ሃይሎች ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ከሃገር ቤት ከተገኘ መረጃ ለመረዳት ተችሏል።
የዩንቨርስቲ ተማሪዎች በኦሮሚያ ክልል እየተፈፀመ ያለው ግድያ እንዲያበቃ ጥያቄን ማቅረብ በጀመሩ ጊዜ በአካባቢው ሰፍረው የሚገኙ የፀጥታ ሃይሎች እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውን ተማሪዎች ገልጸዋል።
አራተኛ ወርን ዘልቆ የሚገኘው ይኸው ተቃውሞ ሰሞኑን በምስራቅና ምዕራብ ሃረርጌ አካባቢ ዳግም ማገርሸቱ የሚታወስ ሲሆን የፀጥታ ሃይሎች በነዋሪዎች ላይ የድብደባና የእስር እርምጃ መውሰዳቸው ታውቋል።