በአዲስ አበባ ከፍተኛ የውሀ እጥረት ተከሰተ
ዘገቢያችን እንደገለጠው በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ካለፈው አንድ ሳምንት ጀምሮ ውሀ የሚባል ነገር የለም። በገርጂ፣ አቃቂ ፣ አዲሱ ገበያ፣ መገናኛና በሌሎችም አካባቢዎች ነዋሪዎች ለመጠጥ የሚሆን ውሀ አጥተው ተቸግረዋል።
የአዲስ አበባ መስተዳዳር የውሀ ባለስልጣናት ችግሮች መከሰታቸውን አምነው፣ ችግሮቹ የተፈጠሩት አንዳንድ የማስተላለፊያ
መስመሮች በመበላሸታቸውና ክረምቱ ማለቁን ተከትሎ የውሀ እጥረት በማጋጠሙ ነው። እንደ ባለስልጣኖቹ ገለጣ ችግሮቹ በአብዛኛው
በሚቀጥሉት 2 ወራት ውስጥ ይፈታሉ።
25 በመቶ የሚሆነው የአዲስ አበባ ህዝብ የንጹህ መተት ውሀ ተጠቃሚ አለመሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።
2011-11-08