ታኀሳስ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አዋጁ በተለይ ወደአረብ አገራት የሚሄዱ ኢትዮጵያዊያን ቢያንስ ስምንተኛ ክፍል እንዲያጠናቅቁና በሚሰማሩበት መስክ ቢያንስ የሶስት ወራት ተጨማሪ ስልጠና እንዲወስዱ ያስገድዳል።
በተጨማሪ ከኤጀንሲዎች ውጪ በግል ግንኙነት ስራ ዜጎች ቢያገኙም እንዳይቀጠሩ ይከለክላል።
አዋጁ በተለይ የትምህርት እድል ያላገኙ በገጠር የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያንን በውጭ አገር እንኩዋን ሰርተው እንዳይበሉ ያደርጋል በሚል ነቀፋ ሲሰነዘርበት ቆይቶአል። እነዚህ ተቺዎች መንግስት ለዜጎቹ እኩል የስራ እድል
ማመቻቸት አለበት ካሉ በሀላ ያልተማሩ ሴቶችም በቂ የተግባር ስልጠና በመስጠት ቢሰማሩ ውጤታማ የማይሆኑበት ምክንያት የለም ሲሉ ይከራከራሉ።በዚህም ምክንያት አዲሱ አዋጅ ህገወጥ ፍልሰትን ከማበረታት ያለፈ ፋይዳ የለውም ሲሉ ተችተውታል።
እንዲሁም በኢትዮጵያና በሰራተኛ ተቀባይ አገራት መካከል የሁለትዮሽ የስራ ስምሪት ስምምነት ከሌለ የስራ ቅጥር መከልከሉ ዜጎች ሰፊ የስራ አማራጭ እንዳይኖራቸው ያደርጋል በሚል ቅሬታ ሲቀርብበት ቆይቶአል።