ጥቅምት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዛንቢያ መንግስት በሕገወጥ መንገድ ወደ አገሬ ገብተዋል በማለት ይዞ አስሮ ያቆያቸውን ስደተኞች ወደየአገራቸው መመለሱን ያስታወቀ ሲሆን ከእነዚህ ተመላሽ ስደተኞች ውስጥ ሰባቱ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውንና ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት በመሸጋገሪያነት በዛንቢያ ለማቋረጥ ሲሞክሩ በጸጥታ ኃይሎች ተይዘው መታሰራቸው ተገልጿል።
የቅጣት ጊዜያቸውን አጠናቀዋል ያላቸውን 7 ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ 2 ሶማሊያዊያን፣ 3 ቡሩንዲዊያን፣ 4 ታንዛኒያዊያን እና 3 ኡጋንዳዊያን በድምሩ 19 አፍሪካዊያን ስደተኞች ሲሆኑ ወደየትውልድ አገራቸው መላካቸውንና ሕገወጥ ስደተኞችን በማዘዋወር የተከሰሱ 3 የአገሪቱ ዜጎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን እንደቀጠለ አስታውቆ በተጨማሪም በሕገወጥ መንገድ ወደ አገራችን ገብተዋል ያላቸውን ሁለት ቻይናዊያንና በሕገወጥ የተጨበረበረ ፓስፖርት በመጠቀም ወደ ዛምቢያ የገቡ ሶማላዊያንና የኮንጎ ዜጎች አስሮ ለፍርድ ማቅረቡን ታይም ኦፍ ዛንቢያ አክሎ ዘግቧል።