ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኦህዴድ ላለፉት 2 አመታት ከተማዋን ሲመሩ የነበሩትን አቶ አብርሃም አዱላን ወደ ክልል ቢሮ በማዛወር የሻሸመኔ ከንቲባ የሆኑትን ለከተማዋ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።
አዲሱ ከንቲባ በሻሸመኔ የሚገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን በማሰቃት የሚወነጀሉ ሲሆን፣ ለአዳማ የተወሳሰበ ችግር መፍትሄ ያመጣሉ ተብሎ እንደማይታመን ምንጮች ይገልጻሉ። ነባሩ ከንቲባ፣ በደባል ሱሶች በመጠመድ ያለፉትን ሁለት አመታት ይህ ነው የሚባል ስራ ሳይሰሩና ጽህፈት ቤታቸውም በወጉ ሳይገቡ ከከንቲባነታቸው መነሳታቸውን ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ተናግረዋል።
በየጊዜው ከንቲባ የሚቀያየሩላት አዳማ፣ ከቤቶች ግንባታና ከመሬት ወረራ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ችግር አለባት። ሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግሮችም በከፍተኛ ሁኔታ ተስፋፍተው የሚገኙባት ከተማ ናት። የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚገልጹት፣ የማህበራዊ አገልግሎት አሰጣጡ ከመቼውም ጊዜ በላይ በመበላሸቱ፣ ህዝቡ በከንቲባውና በሌሎችም ባለስልጣናት ላይ አቤቱታ ሲያቀርብ ቆይቷል።