የኢትዮጵያን ጦር በሶማሊያ መቆየትን ለውይይት ያቀረቡ ጋዜጠኞች ታሰሩ

መስከረም ፳፭ (ኅያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዩኒቨርሳል ቲቪ ጋዜጠኞች የታሰሩት፣ ሁለት የፓርላማ አባላትን ጋብዘው የኢትዮጵያ ጦር በአገሪቱ ውስጥ መቆየት አለበት የለበትም የሚል ክርክር በማድረጋቸው መሆኑን የጣቢያው የዜና ክፍል ሃላፊ የሆነው ጋዜጠኛ አብዱላዚዝ ኢብራሂም ሙሃመድ ተናግሯል።
በርካታ የሶማሊያ ዜጎች የኢትዮጵያ ጦር በሶማሊያ መቆየቱን መቃወም ጀምረዋል። ሟቹ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አልሸባብን በ2 ሳምንታት ውስጥ ደምስሰን እንወጣለን ቢሉም ፣ ጦሩ ግን ያለፉትን 10 አመታት በሶማሊያ ለማሳለፍ ተገዷል።
ጦሩ አገሪቱን ለቆ የሚወጣበት ቀን በውል አይታወቅም። አልሸባብ ተዳክሞ ቢገኝም፣ ሙሉ በሙሉ ባለመጥፋቱ አሁንም ለሶማሊያ መንግስት ስጋት ሆኖ ቀጥሏል።