ሐምሌ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ከምድረ ገጽ ጠፍቶ የነበረው ጊኒ ዎርም በሽታ እንዳዲስ ማንሰራራት መጀመሩ በአዲስ አበባው ሀገር አቀፍ የጤና ጉባኤ ላይ ተገልጿል፡፡
ዶ/ር ዳዲ ጅማ ፣ በኢትዮጵያ በሽታው በደቡብ ክልል እና በጋምቤላ በፍጥነት በሰዎች ላይ መታየት መጀመሩን የጤና ባለሙያዎችን መረጃ ዋቢ በማድረግ ወቅታዊውን ሪፖርት ከጥናታቸው ጋር አዛምደው አቅርበዋል።
በጥቅምት 2011 የመከረው የአለም የጤና ጉባኤ ጊኒ ወርም ላይ ጠንክረው በመስራት ከሀገራቸው ያስወጡ ብርቱ ሀገራት ሲል ለአለም ካበሰራቸው ሀገራት መካከል ኤርትራ ፤ ብሩንዲ፤ ቶጎና ቡርኪናፋሶ ይገኙበታል።
192 ሀገራት ከጊኒ ወርም ነጻ የሚል ሰርተፍኬት ሲሰጣቸው፣ ኢትዮጵያ ግን ሰርተፊኬቱን አላገኘችም።
ድህነትና የንፁህ መጠጥ ውሃ እጥረት ለበሽታው መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረጉ ነው።