የመሳሪያ ትግሉን የህዝብ ብሶት የወለደው ነው ሲሉ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ተናገሩ

ሐምሌ ፺፻ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሰማያዊ ፓርቲ ሊ/መንበር ኢንጂነር ይልቃል የፓርቲያችሁ አባሎች የትጥቅ ትግልን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ በመርህ ደረጃ ኢህአዴግን ብሶት ከወለደው ሰው ጠመንጃ የማያነሳው ለምን ድነው ሲሉ ጠይቀዋል። ሰው መኖር ካልቻለ ምን አማራጭ አለ ሲሉ የጠየቁት ኢ/ር ይልቃል ሰው መቀመጫ መሄጃ ሲያጣ ቢሀድ ምን ይገርማል፣ አትሂድስ ለምን ይባላል? ብለዋል። እንዴውም ወጣቱ ባይሄድ ነው የሚገርመኝ ያሉት ኢ/ር ይልቃል፣ “አከርካሪ ያለውና እውነት የሚናገር ሰው እዚህ አገር አይኑር ተብሎአል ሲሉ የችግሩን መጠን አስረድተዋል። ኢህአዴግ የሚከተለው አካሄድ ለእነሱም አይጠቅምም ፣ አገራችንንም ይጎዳል በማለት ስርአቱ መንገዱን እንዲያስተካክል መክረዋል።