የአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ጦር በደቡባዊ ምዕራብ ሶማሊያ ባካሄደው የሽምቅ የደፈጣ ውጊያ ሰባት የአልሸባብ ታጣቂዎችን መግደሉን አስታወቀ

ሐምሌ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ሰሜናዊ ምዕራብ 302 ኪሎ ሜርት ‘ርቀት ላይ በሚገኘው በዋጅድ አውራጃ ልዩ ስሙ ቦቆል ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ማክሰኞ ዕለት የጦር መሳሪያ ያነገቡ የኢትዮጵያ ወታደሮችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች በከተማዎች ውስጥ ሲርመሰመሱ መታየታቸውን የዘገበው ሆርስድ ሚዲያ፣ በወታደሮቹ ላይ ጥቃት ለመፈጸም የሞከሩ 7 ወታደሮች መገደላቸውን የሰድሩ አውራጃ ምክትል ከንቲባ አደን አባርዬ ለቪኦኤ ገልጸዋል። አልሸባብ በደፈጣው ውጊያ ከፍተኛ ድል ማግኘቱንና በርካታ ወታደሮችን መግደሉን ቢያስታውቅም ጉዳት ስለደረሰባቸው ወታደሮች በአሀዝ አልገለጸም።
ባለፈው ወር አልሸባብ ባደረገው የደፈጣ ውጊያ ሰላሳ የኢትዮጵያ ወታደሮች በዚሁ ክልል ተገድለዋል። ።የረመዳን ወር ፆምን ተከትሎ አልሸባብ በደቡባዊ ሶማሊያ ጥቃቱን አጠናክሮ መቀጠሉም ተዘግቧል።