በጋዛ በሃማስ እንደታገተ የሚነገርለት ኢትዮ – እስራኤላዊ አድራሻው መጥፋት ዘረኝነት ነው ተባለ

ሐምሌ ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የ 26 ዓመቱ ወጣት መንግስቱ አቭራ ከመስከረም ወር ጀምሮ ያለበት አድራሻ አይታወቅም ፤ የእስራኤል መንግስትም ወጣቱን ለማፈላለግ ያደረገው ጥረት አለመኖሩ ዘረኝነት ነው ተብሎአል።
በጋዛ በሃማስ እጅ እንደታገተ የሚነገረው ወጣት መንግስቱ፣ ቤተሰቦች “ልጃችን ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ አልቻልንም ፣ መንግስትም ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ የወሰደው ምንም ዓይነት እርምጃ አለመኖሩ ቅሬታ” ፈጥሮብናል ይላሉ።
የጠቅላይ ሚንስቴር ኔታንያሁ ቃል አቀባይ በበኩላቸው ”ይሄ ከቆዳ ቀለም ልዩነት ጋር በፍፁም አይገናኝም” ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል።የኢትዮ እስራኤላዊ ማኅበረሰብና ቤተሰቦቹ ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ ታጋቹን ለማስለቀቅ ጣልቃ እንዲገባ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ሲል ዘ ጄሩሳሌም ፖስት ዘግቧል።