ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰኔ አንድ ተጀምሮ ሰኔ 20 የሚጠናቀቀው ግምገማ ከፍተኛ አመራሮችን፤አዛዦችን እንዲሁም ተራ የፖሊስ አባሎችን አካቷል።
ከጉለሌ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው የግምገማው ይዘት በፖሊስ ስነምግባር ዙሪያ ነው። በግምገማው ወቅት አንድ ባለ ሳጅን ማዕረግ ያለውና አንድ ኮንስታብል ፖሊስ በስልካቸው ውስጥ የግንቦት ሰባት፤የሰማያዊ ፓርቲና
የሌሎች ተዛማጅ ድርጅቶች መረጃዎች በስልካቸው ውስጥ ተገኝቷል በሚል ተይዘው ወደ ማዕከላዊ ምርመራ ተወስደዋል። ለሌሎች መቀጣጫ ይሆን ዘንድ በግምገማው ላይ ለፖሊሶች እንደተገለጸላቸው ምንጮች አስረድተዋል፡፡