ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች ግንቦት 19/2007 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ አሉኝ ባላቸው ሲ.ዲዎች እና ቀሪ
ምስክሮቹ ላይ ብይን ሰጥቷል፡፡
ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ ምስክሮቹን ለማቅረብ በተደጋጋሚ የሰጠውን እድል ባለመጠቀሙ እና ምስክሮቹን ላለማቅረቡ የሰጠው ምክንያትም በቂ ባለመሆኑ አቃቤ ህግ ያቀረበውን የተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ፍርድ ቤቱ ሳይቀበለው መቅረቱን
ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል።
ተከሳሾች ጥያቄያቸውን ለፍርድ ቤቱ ለማስረዳት በሞከሩበት ጊዜ ፍርድ ቤቱ ‹‹ስነ-ስርዓት አድርጉ!›› በማለት ሊያስቆማቸው ሲሞክር፣ ጻሀፊ አቤል ዋበላ ‹‹እናንተ ራሳችሁ ስነ-ስርዓት አድርጉ….እንናገርበት! ይህ የመብት ጉዳይ ነው…
በግልጽ ችሎት ላይ ህገ መንግስታዊ መብታችንን አክብሩ እንጂ…ጥያቄ አለን ተቀበሉን›› ብሎ በመመለሱ ችሎት በመድፈር ወንጀል ተከሷል፡፡ በዚህም ፍርድ ቤቱ በአቤል ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ለግንቦት 25/2007 ዓ.ም ቀጠሮ
ሰጥቷል፡፡