በዞን ዘጠኝ ጸሃፊዎች ላይ ምስክሮች ቀረቡ

ሚያዝያ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእስር ላይ በሚገኙ ዞን ዘጠኝ በሚል መጠሪያ ስም በሚታወቁት ወጣት ጸሃፊዎች ላይ ምስክሮች ቀርበው ፣ የክሱን ጭብጥ በደንብ በማያስረዳና ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት የሌላቸውን ነገሮች በመናገር ማሳለፋቸውን ችሎቱን የተከታሉት ታዛቢዎች ገልጸዋል።
ችሎቱን ለመከታተል የታደሙ ታዛቢዎች ምስክሮች ሲንተባተቡ እያዩ ችሎት ውስት ይስቁ እንደነበር ታዛቢዎች ገልጸዋል።
ወጣት ጸሃፊዎቹ በማእከላዊ እስር ቤት ድብደባ እንደተፈጸመባቸው መናገራቸው ይታወቃል።