ሚያዝያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያን ወራሪውን የጣሊያን ጦር ድል ያደረጉበት 74 ኛ አመት በአዲስ አበባ ጀግኖች አባት አርበኞች በተገኙበት ተከብሯል።
በአድዋ ጦርነት ወቅት ሽንፈትን የተከናነበው ጣሊያን፣ ከ40 አመት በሁዋላ ራሱን በዘመናዊ መሳሪያ፣ በገንዘብና በሰው ሀይል አደራጅቶ ኢትዮጵያን ቢወርም፣ አባት አርበኞች ለ5 አመታት በዱር በገደሉ ባደረጉት ተጋድሎ፣ የፋሽስት ሙሶሎኒን ጦር ድል በማድረግ የአገራቸውን
ነጻነት አስመልሰዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነጻነቱዋን በራሱ እጅ አስከብራ የቆየች ብቸኛ አገር ናት።